ከስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ከሆኑት ከክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር የተላለፈ የምስጋና ማልዕክት።
ከስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ከሆኑት ከክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር የተላለፈ የምስጋና ማልዕክት።
የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊና የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር በዛሬው ዕለት የለውጡን 8ኛ ዓመት አስመልክቶ በወራቤ ከተማ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለተሳተፉ አካላት በሙሉ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ።
ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ባስተላለፉት መልዕክት በዛሬው ዕለት በወራቤ ከተማ በተካሄደው ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የወራቤ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በወራቤ ከተማ አስተዳደር ዙሪያ የሚገኙ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች (ሳንኩራ ፣አለም ገበያ ከ/አ፣ሁልባራግ፣ዳሎቻ፣ስልጢ፣ቅበት ከ/አ፣የአልቾ ፈረሰኞች) የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ያደረጉት ትዕይንት የአንድነትና የጽናት መገለጫ እንደነበረ በመግለፅ በተለይ በፓርቲው ላይ ያላቸውን ፅኑ እምነት ያሳዩበት ነበር ብለዋሉ።
ይህ የሕዝብ ንቅናቄና ደማቅ ተሳትፎ ማህበረሰቡ በብልጽግና ፓርቲ ላይ ያለውን ጽኑ እምነትና ለለውጡ መንግስት ያለውን የማይነጥፍ ድጋፍ በተግባር ያሳየበት መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።
ይህ ሰልፍ ባማረ እና በደመቀ መልኩ እና በሰላም እንዲጠናቀቅ ተሳትፎ ያደረጋችሁ እና ሌት ተቀን የደከማችሁ አመራሮች፣ የፀጥታ ኃይሎች ፣ባለሀብቶች፣የንግዱ ማህበረሰብ፣ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣የሚዲያ አካላት፣የሰልፉ ድምቀት ለነበራችሁ የወራቤ ከተማ ነዋሪዎች ፣ ዙሪያ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች እንዲሁም ለሰልፉ መሳካት የላቀ ሚና የተጫወታችሁ በሙሉ ፕሮግራሙ በሰላም እንዲጠናቀቅ ስላደረጋችሁ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉ ገልፀዋሉ።
ክብርት ወ/ሮ ነኢማ በመልዕክታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደገለፁት ዛሬ በአደባባይ ያሳያችሁን የማይናወጥ አንድነትና ፍቅር ሳይቋረጥ፣ በቀጣይ በሚኖሩን መደበኛ እና በምርጫ ስራዎች ወቅቶች ከጎናችን በመሆን በሁሉም ዘርፍ ድጋፋችሁ ተጠናክረዉ እንዲቀጥል በአክብሮት እጠይቃለሁ ሲሉ ገልፀዋሉ።